top of page

   የመረጃ ስብስብ

እ.ኤ.አ. ሚያዚያ ወር 2012  ላይ ስለ ዓለም ህዝብ ቁጥር  አንድ አለም አቀፍ ሪፖርት ወጥቶ ነበር ፡፡ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ሰዐት የዓለም ህዝብ ቁጥር 7 ቢሊዮን ገደማ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ከዚህ ውስጥ 750 ሚሊዮን ወይም 11% የሚሆነው ህዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት  የሚያምን፣ 2.6 ቢሊዮን የዓለም ህዝብ ወይም  38%  ገደማ የሚሆነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የሰማ ነገር ግን ያልተቀበለ  / ሌሎች አዳኞች አሉ! ብለው የሚያምኑ/ ፣ የተቀረውና ሰፊው ህዝብ ማለትም 3.5 ቢሊዮን ወይም  50% ገደማ የሚሆነው ምንም የወንጌል መልዕክት ያልሰማና የክርስቶስን አዳኝነት ያልተቀበለ ነው፡፡

በቅርብ የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው  በምንኖርባት ፕላኔት ላይ  ከሚገኙ 11,640 ብሔር ብሔረሰብ መካከል 6,734 ገደማ የሚሆነው ወንጌል ያልደረሰው እንደሆነ ታውቋል፡፤ ይህ ማለት መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሑፎች በቋንቋቸው ያልተተረጎመላቸው፣ በቋንቋቸው የሚመሰክርላቸው አገልጋይ የሌላቸው ናቸው፡፡ይህ ባለሆነበት ሁኔታ ደግሞ ቃሉን የሚካፈሉበት ቤተክርስቲያን አላቸው ብለን አንጠብቅም፤ እንደዚህ ያለውን ዜና ስንሰማ ልባችን ይነካል፡፤

 

 

  በምድራችን ኢትዮጵያ ላይ በተመለከተ እግዚአብሔር የረዳቸውና  የተለያየ የወንጌል እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ባለ ራዕዮች አልጠፉም፡፡አንዳንዶቹ በዩንቨርስቲ እና በኮሌጅ ለሚማሩ ተማሪዎች የወንጌል ሸክም ያነገቡ ሲሆን፣ ሌሎች ገና በማደግ ላይ ላሉ ህጻናት ከስር ኮትኩተው ለማሳደግ ሸክም የተሰጣቸው፣ ሌሎች በአባት ጡረተኞች፣ የጎዳና ላይ ተደዳሪዎች፣ አሁን አሁን ደግሞ ገዳማት ላይ፣ ሴቶች ላይ፣ ባለ ስልጣናት ላይ፣ እስር ቤት ላይ፣ ነጋዴዎች ላይ፣ እርቲስቶችና ሙዚቀኞች ላይ፣ እስፖርተኞች ላይ፡ በተለየ ሸክም የሚሰሩ ተነስተዋል፡፤ በቅርቡ እንደሰማሁትም በአዲስ አበባ ላሉ ሱማሌያውያን ሸክም ተሰምቷቸው ቋንቋቸውን እያጠኑ ያሉ ወንድሞች እንዳሉ ነው፡፡

    በአንድ ወቅት በግሬት ኮሚሽን ኢትዮጵያ በተደረገው ጥናት መምሪያ ላይ እንደነበብኩት ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ከ83 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች መካከል 33 ያህሉ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ወንጌል ያልደረሳቸውና አንድም አጥቢያ ቤተክርስቲያን ያልተተከለባቸው ቦታዎች እንደሆኑ ነው፡፡ቢያንስ መጽሐፍ ቅዱስ እንኩዋ ገብቶ ለማደል እንዳይቻል በቋንቋቸው የተተረጎመ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር አማካኝነት ወደ ተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች አዲስ ኪዳንንና ሙሉውን የያዘ ለመተርጎም ተሞክሯል፡፡ እስካሁንም ጥረቱ ቀጥሏል፡፡ ቢሆንም ገና ከ ሃምሳ በላይ ብሔር ብሔረሰቦች በቋንቋቸው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲተረጎምላቸው ይጠብቃሉ፡፡

     በዓለም ላይ ከ4,200 በላይ ሐይማኖቶች እንዳሉ Wikipedia, the free encyclopedia ዘግቧል፡፡ በዓለም ላይ በቁጥር አንድ ላይ የተቀመጠው ሐይማኖት ክርስትና ሲሆን ከዓለም ህዝብ 35% /ፐርሰንት/ ያህሉን ማለትም 2.3 ቢሊዮን ገደማውን የያዘ ነው፡፡ በሁለተኝነት የሚከተለው እስልምና 1.6 ቢሊዮን ህዝብ ማለትም 23  %/ ፐርሰንቱን/ የያዘ እንደሆነ ይገመታል፡፡ ክርስትና ስንል በዓለም ላይ ያሉትን ምናልባትም ከ33 ሺህ በላይ ተከፋፍለው ያሉትን ዲኖሚኔሽኖችን ማለት ነው፡፡

የሀይማኖቶች ደረጃ

 

1-ክርስትና     2.3 ቢሊዮን ተከታዮች     35 %.

 

2-እስልምና    1.6 ቢሊዮን ተከታዮች       23 %

 

3-ሂንዱኢዝም   851 ሚሊዮን ተከታዮች    14 %

 

4-ቡዲዝም    375 ሚሊዮን ተከታዮች        6 %

 

5-ሲኪሂዝም    23 ሚሊዮን ተከታዮች        0.36 %

 

6-አይሁድ    14 ሚሊዮን ተከታዮች           0.22 %

 

7-ባሃኢዝም   7.5 ሚሊዮን ተከታዮች          0.1 %

 

8-ኮንፊሽኒዝም    6.4 ሚሊዮን ተከታዮች          0.1 %

 

9-ጄይኒዝም     4.5 ሚሊዮን ተከታዮች           0.1 %

 

10-ሺንቶኢዝም    2.8 ሚሊዮን ተከታዮች       0.0 %

 

 

 

 

 

 

 

akababi
kuankua
  የተለያዩ የወንጌል ሚሲዮናውያንን ምስክርነት እና አድራሻ ለማግኘት እዚህ    ይጫኑ! coming soon

© 2016 by AL Consulting LLC. Proudly created with Wix.com

  • Twitter Classic
  • c-facebook
bottom of page