top of page

  ጌታችን በተሰቀለበት ጊዜ ከጎንና ጎኑ አብረው የተሰቀሉ ወንበዴዎች ነበሩ፡፡ አንደኛው እንደዚህ ብሎት ነበር ፡-" አንተስ ክርስቶስ አይደለህምን ? ራስህንም  እኛንም አድን ብሎ ሰደበው ይላል  !"/ ሉቃ.23፤39/ ይህ  ሰው እንዳሰበው ክርስቶስ ራሱን ካዳነ ለእኛም አያቅተውም የሚል ዓይነት ነው፡፡ ግን መለኮታዊው መርህ  ምን ነበር? ጌታ በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጠን፡፡ በተለይም በመሸነፍ ውስጥ ማሸነፍ እንዳለ ላልተመለከታችሁ የመለኮትን አሰራር እና አደራረግ ትረዱበታላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡እሰቲ መሸነፍና ሞኝነት በሚመስል መንገድ ውስጥ እግዚአብሔር የሚሰጠንን ድል እንለማመድ!!

 

 

 

                                ራሱን ካላዳነ !


                  የመከራዋ ቀን ዘግናኝቱ ሌሊት


                  ልብን ከሚሰነቅሩ ብዙ ቃላት


                  በተለይ በተለይ ራስህን አድን የሚለው


                  ራሱን ካዳነ ይሆን የሚያድነው?


                   በራሱ ሲያሳይ ነው በሰው ሚታመነው?


                   እንዲህ ይሆን ወጉ ያገር ፍልስፍናው?


                   ለራሱ ካልሆነ ለእኛ በምኑ ነው!


                   ግን እኮ ራሱን ካዳነ በዚህች ዕለት


                   መከራ ካልነካው ጂራፍ ካልገረፈው


                   ውሀ  ጥም ካልጠማው ደም ላብ  ካላላበው


                   ሰራዊቶች  መጥተው ከሰማይ ከረዱት


                   ደመኞቹን  መጥተው ከተበቀሉለት


                   ወታደር  ከወታደር ጋር ተጋጭቶ


                   ከሰማይ የመጣው የምድሩን ረትቶ


                   ያለ እስራት ፣ያለ ችንካር ፣ያለ ውርደት


                   በሰው አጠባበቅ እንዲ ነው ጀግንነት::


                   ራሱን ካዳነ ለእኛ ምን ሊያቅተው?


                   ለእኛም ያደርገዋል ለእሱ  እንዳደረገው::


                   ነገር ግን እውነቱ  ያንድዬ ብልሀቱ


                    ድነትን ሲቀምር በአዋቂነቱ


                    ካላዳነ ራሱን መድሐኒት ተገኘ


                    በራሱ ሳያሳይ በእኛ ዝናው ናኘ::


                    እርሱ ተገረፈ እኛ ተፈወስን


                    እርሱ ተሰቃየ እኛ ድል አገኘን::


                     ራሱን ካላዳነ ነበር የሚያድነው


                    መለኮት እንደዚህ ድነትን ቀመረው፡፡

                                                                                                      benjabef@gmail.com

rasunkaladan

ሥርህ የት ነው?

ግንዱስ ይኸው መጋጠሚያ መታጠፊያው

ጠነካከሮ ባለ ቀለም አገዳ አንጓው

ሰፋፊ ቅጠሉ ከነበዙት ቅርንጫፎች

አቤት ደስ ያሰኛል ለየተመልካቾች

ግና ሥርህ የት ነው? የቱ ጋር መነሻህ

የነገህ ማረፊያ መዳረሻ ዋጋህ

የት ድረስ ነው ሩጫህ ? የርዝመትህ ልኩ

እንዲህ ዳማረብህ የመሔጃህ ጥጉ::

እርሱ ማንነትህ የነገህ መስፈሪያ:

ሥርህ ሥራ ስርህ መጎሪያ መኖሪያ::

ብትቆፍረው የት ነው ? ስንት ሜትር ርቋል?

ወደ ላይህ ሳይሆን ሥርህ የት ይደርሳል?

የመገኛህ ምንጩ የበቀልክበቱ:

ትቢያና ኮልኮሌን አልፈህ የወጣህበቱ፡፡

ሥርህ ምን ይመስላል? ያንተ መሰረቱ:

ከርዝመት፣ ከቁመት፣ ከስፋት በፊቱ፡፡

© 2016 by AL Consulting LLC. Proudly created with Wix.com

  • Twitter Classic
  • c-facebook
bottom of page