top of page

   ፋሲካ


 

    ለብርሃነ ትንሳኤው እንኩዋን አደረሳችሁ!

'' ወይቤሉን ፡ አትደንግፃ፡፡ ኢየሱስሃኑ፡ ናዝራዊ፡ተኀሥሡ፡ ዘተሰቅለ፡፡ ተንሥአ፡ ወኢሀሉ፡ ዝየስ፡ ወናሁ፡ መካኑ፡ ኀበ፡ ተቀብረ፡፡ ''

 /እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፡ አትደንግጡ፡ የምትፈልጉት የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ነው፡ እርሱ ተነስቶአል፡ እዚህ የለም፡ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ ይኸውላችሁ፡፡/ ማርቆስ 16፤6

 ጌታችን ፣ መድኀኒታችን ና አምላካችን  ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሁላችን በደል እና ሐጢያት መከራን ተቀብሎ በመስቀል ላይ ከሞተ በሁዋላ ፡ በሶስተኛው ቀን ከሞት ተነስቶአል፡፡ ይህ ብርሃነ ትንሳኤው ነው በመላው ዓለም የፋሲካ በዐል ተብሎ  የሚታወቀው ፡፡

ፋሲካ የስሙ ትርጉዋሜ ማለፍ  ማለት ሲሆን፤ ይህም እስራኤላውያን ከ 430 በግብጽ በባርነት አገዛዝ ከነበሩበት አሰጨናቂ ዓመታት ነጻ የወጡበት ቀን ነው፡፡ በዚያም ቀን ምሽት በሁሉ ቤት ታርዶ የነበረው ጠቦት ፣ በበራቸው ጉበንና በመቃናቸው የለቀለቁት ደም ምሳሌነቱ ክርስቶስና የክርስቶስ ደም ነው፡፡ጌታችን እኛን ከሐጢያትና ከኩነኔ ሊያድነን ዋጋ ከፍሎአል፡፡ አሁን በአዲስ ኪዳን ዘመን ከ ዓለም ልንወጣ የምንችለው ደግሞ የአዲስ ኪዳኑን / የፋሲካውን በግ / በማመንና በመቀበል ሲሆን ፣ በቀራኒዮ በፈሰሰው ደሙም ከሚመጣው ቁጣ ማምለጥ እንችላለን፡፡ ደሙን በጉበኑ ባላደረገ ቤት ሁሉ ሞት እንደነበረ፡ በክርስቶስ ደም ያልነጻ እና የደሙ ማህተም በግንባሩ የሌለ ማንኛውም ሰው ከዘላለም ሞትና ፍርድ ማምለጥ አይችልም፡፡

እርሶም ዛሬ ከግብጽ  / ከዓለም / ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በክርስቶስ አምልጠው አውነተኛውን የክርስትና ህይወት ሊኖሩ የሚወስኑበት ጊዜ እንዲሆን እመኝልዎታለሁ፡፡ በዛሬዋ ቀን በመስቀል ላይ ስለ እርሶ ሞቶ የተነሳውን ጌታ ና መድሓኒት በልብዎ ውስጥ ስፍራ ይስጡት፡፡ እስቲ የቀረዎትን  ዘመን ለሞተውና ለተነሳው ጌታ ሊሰጡት ዛሬ ይወስኑ! እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይረዳዎታል፡፡

                                                                              መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንልዎ!!!  

  ማስታወሻ፡-  ይህንን መልዕክት ፋሲካውን እያከበሩ ላሉ ወዳጅ  ዘመዶቻችን ሁሉ ሼር እናድርግ!

fasika

የክርስቶስ  ልደት   /ገና/

 

አስቀድሜ እንኩዋን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዐል በሰላም አደረሳችሁ እላለሁ፡፡

      ''እነሆ ለህዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምስራች      እነግራችሁዋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት  ከተማ  መድሐሀኒት  እርሱም  ክርስቶስ  ጌታ  የሆነ ተወልዶላችኃልና.....''ሉቃ.2፤11

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ለሰው ልጆች ሁሉ መልካም ዜና ነው፡፡እርሱ የዓለምን ሁሉኀጢይት ለማስወገድ ተወለደ፡፡መለዐኩ ቅዱስ ገብርኤል ለቅድስት ማርያም እንዳበሰረው ''....ስሙን  ኢየሱስ ትዬዋለሽ እርሱም  ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል.." የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ቀ. 32  ፡፡

ምናልባት ብዙ ጊዜ በተለምዶ ብቻ ገናን ማክበር እየተስፋፋ የሄደ ጉዳይ ነው፡፡ ፈረንጆቹ  በልደቱ  ቀን ስጦታን መለዋወጠ፤ዛፎችን በደመቀ መብራት ማሸብረቅ፤መብላት እና መጠጣት የመሳሰሉትን ጉዳዮች በመፈጸም ቀኑን ያሳልፋሉ፡፡ከበዛ ደግሞ ሳንታ ክሎስ ብለው ከሰየሙት የገና አባት ጋር ፎቶ መነሳት ህጻናቶችን  ማስደሰት....የመሳሰሉትን ያደርጋሉ፡፡እንደውም አሁን አሁን ገና ማለት የልጆች ጊዜ ለማድረግ ትንሽ የቀረው ይመስላል፡፡ይህ ማለት ከዋናው ጉዳይ ጋር እየተለያየን ነው ማለት ነው፡፡

በአገራችንም ከዚህ ባልተናነሰ ሁኔታ ባህላዊ ምግቦችን በማዘጋጀት እና የገና ዛፎችን በማስጌጥ ሲዘፈን ሲጨፈር መዋል የተለመደ ነገር ሆኑዋል፡፡ብቻ በሁሉም ጎን ማለት ይቻላል ፈር የለቀቀ ጉዳይ ይስተዋላል፡፡ማለትም ከዋናው ጉዳይ ጋር ያለተገናኙ ነገሮች የበዐሉ ዋና ነገር ሆነው ቀርበዋልና፡፡

ከርስቶስን  ከውልደቱ ጀምሮ ሊገድለው ሲፈልግ የነበረ ሰይጣን፤ በሁዋላም ከሞት መነሳቱን በውሸት ዜና ተክቶ አልተነሳም ብለው እንዲናገሩ ሲጥር የነበረው ሰይጣን፤ አሁን ደግሞ ስልቱን ቀይሮ ሰዎች የገናን ትክክለኛ ነገር እንዳይረዱ በማድረግ በሚችለው ሁሉ እየሰራ ይገኛል፡፡በተወሰነ መልኩ የተሳካለትም ይመስላል፡፡

የልደቱን ባለቤት በቅጡ ያልተረዳ ህዝብ ገናን ቢያከብር ለሰይጣን የራስ ምታት አይደለም ፡፡ ብዙዎች ክርስቶስን ለሌላ ሀይማኖት እየሰጡ: ከልብና ከቤት አስወጥቶ  ፤ደግሞ  ሌሎች ምናልባት ያልተቀበሉትን የኢየሱስን ልደት ለማክበር ደፋ ቀና ማለት ምን ያህል ያለማስተዋል ይሆን ? ምዕመናን  ሆይ  ልብ ልንል የሚገባው ዋና ነገር የተወለደው ክርስቶስ በእኛ ልብ ስለመኖሩ እና የተወለደበት፣የተሰቀለበት፣የሞተበትንና፣የተነሳበት ትክክለኛ ዓላማ ገብቶናል ወይ የሚለው ቁም ነገር ነው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከሐጢያት ለማዳን ተወለደ፤በእርሱ የሐጢያታችንን ስርየት እናገኛለን /የሐዋርያት ሥራ.10፤43/፤ መጽሐፍ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላል፡፡ ሮሜ 10፤11

እርሱ  የህይወታችንም  የክርስትናችንም መሰረት ነው፡፡ ያውም በልደቱ  ቀን እርሱን ደስ የማያሰኘውን ጉዳይ  እየፈጸምን እርሱን አስወጥተን ወይም ቸል ብለን ድግሱ ላይ ብቻ የምናተኩር ከሆንን ምኑ ላይ ነው ክርስትናው?  ያስብላል፤

እህቶቼና ወንድሞቼ አባቶቼና እናቶቼ ምንም እንኩዋ ብዙ ዓመታት ሳይገባን ያደረግን ቢሆን አሁን ግን ወደ እውነት እንመለስና ትክክለኛውን ልደት እናክብር ንስሐ እንግባ፣በደሙም ፊቱ በመቅረብ እንቀደስ፡፡

ልብዎ ፈቃደኛ  ከሆነ ቀጥሎ ያለውን ጸሎት ይጸልዩ፡-እግዚአብሄር ሆይ አንድያ ልጅህን ወደ ዓለም ልከህ ስለ እኔና ስለ ዓለም ሐጢያት እንዲወለድ ስላደረግህ አመሰግንሀለሁ፡ከልጅነት እስከ ዕውቀት የሰራሁትን መተላለፍና ሐጢያት ይቅር በለኝ፡፡ጌታ  ሆይ ወደ ልቤ እንድትገባ እፈቅድልሀለሁ ሁለጊዜ አንተን በማመን ጸንቼ እንድኖር እርዳኝ በጌታችን በመድሀኒታችን በኢየሱስ ክርሰቶስ ስም አሜን፡፡

Gena

አዲሱ ዓመት

 

እንኳን አደረስዎ !

 

‹‹በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል፡፡ የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፣ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ፡፡›› መዝ.65፡11

ገና በዘፍጥረት ወራትንና ዘመናትን ደግሞ ወቅቶችን እንድንለይ ብርሀናትን በሰማይ ያደረገልን እግዚአብሔር ነው፡፡/ዘፈፍ.1፡14 ነና 15/፡፡ እነሆም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ዓመታቶች እየተቆጠሩ አለ፡፡ ያለፈው ዓመት ለእርሶ እንዴት ነበር ? አንዳንድ ጊዜ የሀዘን፣ የመከራ፣ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ሌላ ዓመት ደግሞ ልንረሳቸው የማንችላቸው ትልልቅ ስኬቶች በህይወታችን የሆኑባቸው ጊዜዎች ይሆኑልናል፡፡ የሆነው ሆኖ እግዚአብሔር በሰላም ወደዚህ አዲስ ዘመን አሸጋግሮናልና ክብር ምስጋን ለእርሱ ይገባዋል፡፡ ምናልባት ባለፈው ዓመት ሊሰሩ ፈልገው ያልሰሩት፣ ሊማሩ ፈልገው ያለተሳካልዎ ቢሆን ወይም ሌሎች በእንጥልጥል ላይ ያሉ ዕቅዶች ቢኖርዎ ፤ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ዘነድሮ ያደርጉታል፡፡ ሁልጊዜ መረሳት የሌለበት ነገር ግን በህይወታችን የፈለገውን ዓይነት ዕቅድ ቢኖረንም እንኳ ልንተገብር የምንችለው እርሱ ከፈቀደልን ብቻ ነው ፡፡ ለዚህም ነው በቃሉ ላይ ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ይህንና ያንን እንደርጋለን በሉ የተባለው፡፡ያዕ.4፡15

ስለ መንፈሳዊ ነገርዎስ ሲያስቡ ያላደረጉትና የሚቆጭዎት ነገር ይኖር ይሆን? እስኪ በዚህ ጊዜ ላይ ግን ቆም ብለው ያስቡ በቸርነቱ ዘመን የጨመረልዎትን ጌታ አክብረው ለማለፍ ቀሪ ዘመንዎትን ይስጡት የሚያደርጉት ሁለት በጣም ቀላል ነገሮችን ነው፡፡ ይሁንና ይህንን በማድረግዎ ዘላለምዎትን ሁሉ ይቀይራሉ፡፡

       1ኛ-ንስሐ መግባት ፡- እስኪ ቀጥለው እንዲህ ብለው ንስሐ ይግቡ ፡፡ 1ዮሐ.1፡9

          - ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ባለፉት ዓመታቶች ሁሉ በቸርነትህ ስለሰጠኸኝ ና ስላደረክልኝ ነገሮች ሁሉ አስቀድሜ አመሰግንሀለሁ፡፡ ይሁንና እኔ ግን ታማኝ ሆኜ አንተን የሚያስደስትህን ሁሉ አላደረኩም፡፡ በስህተት ና በድፍረት የሰራሁትን ሐጢያት ሁሉ ይቅር በለኝ፡፡ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከበደሌ ሁሉ አንጻኝ፡፡ አሜን፡፡

     2ኛ- ማመን፡- ምን ብለው ነው የሚያምኑት? ሮሜ. 10፡9-10

         - ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ፤ እርሱ ስለ እኔ ሐጢያት ተሰቅሏል ፣ ሞቷል ፣ በ 3ኛው ቀን ተነስቷል ፡፡

 

                                                                              መልካም ዘመን ይሁንልዎ !

newyear

Thanks Giving

 

  Whereas the duty of all nations to acknowledge the providence of Almighty God, to obey his will, to be grateful for His benefits ,and humbly implore His protection ,aid and favors…

Now therefore ,I do recommend and assign the 26th of November next, to be devoted by the people of these  states to the service of that Great and Glorious Being.Who is the beneficent Author of all the good that was ,that is ,or that will be that we may then all united in rendering unto Him our sincere and humble thanks for His kind care and protection of the people of this country , and for all the great and various favors which He has been pleased of confer upon us.

Our founding fathers openly recognized God. They were aware of our need for God if we were to be a healthy nation .George Washington said: ‘’ It is impossible to rightly govern the world without God and the Bible.’’ They know that if the nation was going to work its people needed to voluntarily live by God’s rules.

Times have changed .We may be the only culture in the world that openly acknowledges God in our constitution,on our money , and on Thanks giving, but refused to allow God to be named in any of our public institutions. As a nation we are working hard to push God out of our lives.

Ignoring God isn’t unusual.The history of the world is a story of people turning away from God.Amazing,God hasn’t turned away from us yet.But if we do not repent,He will.

Government can not turn us back to God. Turn back to God requires a change of heart.When get out hearts fixed,our priorities lineup, and things work better.

You can get this change of hearts by giving up your old life and turning to God. He sent His Son Jesus to close this huge gulf between us and God.So when we turn to God in the name of Jesus, we are acceptable as if we never sinned-the Bible calls it being clothed with Jesus’ clothes in front of God. In the name of Jesus you can belong to God and busy yourself in His world. In the name of Jesus you can once again belong to others. When you belong to others, your life won’t be sucked dry –you’ll be like a mountain spring fuller and fresher than you ever imagined.That’s because you keep turning God to fill you up,and He has all the resources in the universe at His command. It’s like being wealthier than you could ever imagine.

So I hope you will turn your face towards God this Thanks giving.Do more than Thank Him for good thanks giving will become a year-round event in your life.

‘’ Blessed is the nation whose God is the Lord: Behold the eye of the Lord is upon them that fear Him, upon them hope in His mercy’’ , Psalm 33: 12,18.

‘’Righteousness exalts a nation, but sin is a disgrace to any people.’’Proverb 14:34.

‘’ For God so loved the world that He gave His only begotten Son that whosoever believeth in Him should not perish, but have everlasting life.’’ John 3:16.

‘’ He that believeth on the Son hath everlasting life: and he that believeth not the Son shall not see life: but the wrath of God abideth on him’’ John 3:36.

‘’ Whosoever shall call upon the name of the Lord shall be saved .’’ Romans 10:13

              Thanks Giving Prayer

Dear God :Thank you for the wonderful gifts you have poured out on our nation.In the name of Jesus,who died for my sins,forgive me and forgive our nation for enjoying your gifts while trying to live without you. I repent of how I have been living and gratefully give my heart to you today. Help others in our nation to turn to you .Amen!

                              Source: from Tract League blog

If you want to read more use this blog: http://tehadesothought.blogspot.com

Thanksgiving

© 2016 by AL Consulting LLC. Proudly created with Wix.com

  • Twitter Classic
  • c-facebook
bottom of page